እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።
በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣ በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።
በኃያል እጅ እንዳሉ ፍላጾች፥ የጐልማስነት ልጆች እንዲሁ ናቸው።
ሰው በወጣትነቱ የሚወልዳቸው ወንዶች ልጆች በወታደር እጅ እንዳሉ ፍላጻዎች ናቸው።
እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም፥ አያንቀላፋምም።
የሽማግሌዎች አክሊል የልጅ ልጆች ናቸው፤ የልጆችም ክብር አባቶቻቸው ናቸው።
እነሆ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አነሣለሁ፤ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ፤ በእርስዋም ላይ ይሰለፋሉ፤ ከዚያም ትወሰዳለች፤ ፍላጾቻቸውም ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ብልህ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው።