ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባዮችሽ ቆሙ።
ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።
ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከጌታ ዘንድ ነው።
ርዳታዬ የሚመጣው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ነው።
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለአግዚአብሔር እልል በሉ።
ቀኝ እጅህን የያዝሁህ፥ እንዲህም የምልህ እኔ አምላክህ ነኝና።
እግዚአብሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆች ይሰናከላሉ፤ አያሸንፉም፤ ለዘለዓለምም የማይረሳ ጕስቍልናቸውን አላወቁምና ፈጽመው አፈሩ።
እስራኤል ሆይ! በመከራህ ጊዜ ማን ይረዳሃል?
አሁንም አምነን፥ “እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንበል።