ረድኤቴ ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ ከአታላይ ምላስም አድነኝ።
ከዓመፀኛ ከንፈር ከሸንጋይም አንደበት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።
እግዚአብሔር ሆይ! ከሐሰተኞችና ከአታላዮች አድነኝ።
የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥ የኀጢአተኛ እጅም አያውከኝ።
መድኀኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤትን ያደርጋል።
ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።
ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፥ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።