የዐመፃን መንገድ ከእኔ አርቅ፥ በሕግህም ይቅር በለኝ፤
ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
ጌታን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።
ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት።
ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” እያሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ እርስ በርሳቸው ያስተዛዝሉ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቤት በተመሠረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያከበሩ በታላቅ ድምፅ ዘመሩ።
በዚያም ዎፎች ይዋለዳሉ፥ የሸመላ ቤትም ይጐራበታቸዋል።
በመንገዳቸው ንጹሓን የሆኑ፥ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ብፁዓን ናቸው።
ትእዛዛትህን እጅግ ይጠብቁ ዘንድ አንተ አዘዝህ።
በስጦታው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና ዐሰብሁ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ወገኖች እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸርነቱና እንደ ጽድቁ ብዛትም ይቅርታውን ያመጣልናል።