ምስክሩን የሚፈልጉ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ብፁዓን ናቸው፤
የእስራኤል ሕዝብ፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።
ቸር እንደሆነ፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም እንደሆነ የእስራኤል ቤት አሁን ይንገሩ።
የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ “የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው” ይበሉ።
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይነግሣል፤ ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው።
ይህን ሕግ ለሚፈጽሙ ሰዎች ሰላምና ይቅርታ ይሁን፤ የእግዚአብሔር ወገኖች በሆኑ በእስራኤል ላይም ይሁን።
በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን?