አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
መክበቡንስ በየአቅጣጫው ከበቡኝ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።
መክበቡንስ ከበቡኝ፥ በጌታ ስም አጠፋኋቸው።
ከየአቅጣጫው በዙሪያዬ ነበሩ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኀይል ደመሰስኳቸው።
ኢዮአብም በፊቱና በኋላው ሰልፍ እንደ ከበበው ባየ ጊዜ ከእስራኤል ጐልማሶችን መረጠ፤ እነርሱም ከሶርያውያን ጋር ተዋጉ።
የኀይላቸው ትምክሕት አንተ ነህና፥ በይቅርታህም ቀንዳችን ከፍ ከፍ ይላልና።
ረድኤታችን ከእግዚአብሔር ነውና። ንጉሣችንም የእስራኤል ቅዱስ ነውና።
ሳኦልና ሰዎቹም በተራራው በአንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በሌላው ወገን ሄዱ። ዳዊትም ከሳኦል ፊት ያመልጥ ዘንድ ተሰውሮ ነበር። ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ከብበዋቸው ነበርና።