እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና።
አሕዛብ ሁላችሁ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ ሕዝቦችም ሁሉ፤ ወድሱት፤
ሃሌ ሉያ! አሕዛብ ሁላችሁ፥ ጌታን አመስግኑት፥ ሕዝቦችም በሙሉ አመስግኑት፥
መንግሥታት ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት! ሕዝቦች ሁሉ አመስግኑት!
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግነው። ሃሌ ሉያ።
እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ እኛም በሕይወት እንኑር
ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥ አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና
ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤትን ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።
ዳግመናም እንዲህ አለ፥ “አሕዛብ ሁላችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ ያመሰግኑታል።”
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።