የሞት ጣር ያዘኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፤ ጭንቀትና መከራ አገኘኝ።
ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
ባሕር አየች፥ ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
ባሕር ይህን አይቶ ሸሸ፤ የዮርዳኖስም ወንዝ ውሃ ማፍሰሱን አቁሞ ወደ ኋላው ተመለሰ።
እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።
የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና።
ውኃንም እንደ ወንዞች አፈሰሰ። ውኃንም ከዓለት አፈለቀ፥
ነገር ግን እርሱን መበደልን እንደገና ደገሙ፥ ልዑልንም በምድረ በዳ አስመረሩት።
ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የአዜብ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፤ ባሕሩንም አደረቀው፤ ውኃውም ተከፈለ።
በቍጣህ እስትንፋስ ውኃው ቆመ፤ ውኃዎች እንደ ግደግዳ ቆሙ፤ ሞገዱም በባሕር መካከል ረጋ።
በሙሴም ቀኝ እጅ ውኃውን ከፈልሁ፤” ውኃውም ተከፍሎ በፊቱ ጸና፤ የዘለዓለም ስምንም አደረገለት።
ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ።