መዝሙር 109:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገድ ከፈሳሽ ውኃ ጠጡ፤ ስለዚህ ራስ ከፍ ከፍ ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ ሆኖ ይገኝ፤ ጸሎቱም ለፍርድ ትሁንበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተምዋገተም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፥ ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተሟገተ ጊዜ ተረትቶ ይመለስ፤ ጸሎቱ እንኳ እንደ ኃጢአት ይቈጠርበት፤ |
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።
በኦሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእርግማን ውስጥ ይኖራሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ የማይፈጽምና የማይጠብቅ ርጉም ይሁን።”