ከከተማዪቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፥ “ተነሥተህ ሰዎቹን ተከትለህ ያዛቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ በመልካሙ ፈንታ ስለምን ክፉን መለሳችሁ?
መዝሙር 109:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በቀኝህ ነው፥ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በበጎ ፈንታ ክፋትን፣ በወደድኋቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመልካም ፋንታ ክፉን፥ በፍቅር ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመልካም ፈንታ ክፉ፥ በፍቅር ፈንታ ጥላቻ ይመልሱልኛል። |
ከከተማዪቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፥ “ተነሥተህ ሰዎቹን ተከትለህ ያዛቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ በመልካሙ ፈንታ ስለምን ክፉን መለሳችሁ?
አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
ለሰውነቴ ጕድጓድን ቈፍረዋል፤ በውኑ በመልካም ፈንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ፥ ቍጣህንም ከእነርሱ ትመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ።
ነገር ግን ይህን የምናገር ስለ ሁላችሁ አይደለም፤ የመረጥኋቸው እነማን እንደ ሆኑ እኔ አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ‘እንጀራዬን የሚመገብ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊዉን ገደለ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ እስራኤልም ሁሉ አይተው ደስ አላቸው፤ በከንቱ ዳዊትን ትገድለው ዘንድ ስለምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ?”