መዝሙር 108:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላዩ ኀጢአተኛን ሹም፤ ሰይጣንም በቀኙ ይቁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣ በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስልንም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትወደው ሕዝብህ ይድን ዘንድ፥ ጸሎታችንን ስማ፤ በኀይልህም ታደገን። |
እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈጣሪዬን የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መልካም ነው” ብለው መለሱ።
የተሰጣቸውን ወይፈንም ወስደው አዘጋጁ፤ ከጥዋትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበዓልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም፤ የሠሩትንም መሠዊያ እያነከሱ ይዞሩ ነበር።
እስከ ሠርክም ድረስ ትንቢት ይናገሩ ነበር፤ ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስና የሚያደምጥም አልነበረም። ከዚህም በኋላ መሥዋዕት በሚያርግበት ጊዜ ኤልያስ ነቢያተ ሐሰትን፥ “እንግዲህስ ወዲያ በቃችሁ፤ ወግዱ፤ ሂዱም፥ እኔም መሥዋዕቴን እሠዋለሁ” አላቸው።
እግዚአብሔር ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የአንበሶቹን መንጋጋቸውን ያደቅቃል።
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።
በሮሜ ላላችሁ፥ እግዚአብሔር ለሚወዳችሁ፥ ለመረጣችሁና ላከበራችሁ ሁሉ፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በዘመኑ ሁሉ ይጋርደዋል፤ በትከሻውም መካከል ያድራል።
እንግዲህ እግዚአብሔር እንደ መረጣቸው ቅዱሳንና ወዳጆች፥ ምሕረትንና ርኅራኄን፥ ቸርነትንና ትሕትናን፥ የውሀትንና ትዕግሥትን ልበሱት።