በጥል ከበቡኝ፥ በከንቱም ተዋጉኝ።
ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ።
በገና ሆይ፥ ተነሥ፥ መሰንቆም እንዲሁ፥ እኔም ማለዳን ልቀስቅሰው።
እግዚአብሔር ሆይ! በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በአሕዛብ መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና።
እግዚአብሔርን የምትወድዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤ እግዚአብሔር የጻድቃኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ፣ እስራኤል ሆይ፥ እልል በል፣ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ በፍጹም ልብሽ ሐሴት አድርጊ ደስም ይበልሽ።
በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፣ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።