መዝሙር 107:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረትህ በሰማይ ላይ ታላቅ ናትና፥ እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንዶቹ ጭው ባለ በረሓ ተቅበዘበዙ፤ ወደሚኖሩባት ከተማ የሚያደርስ መንገድ ዐጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበረሃ፥ በምድረ በዳ ተቅበዘበዙ፥ የሚኖሩበትንም ከተማ መንገድ አላገኙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንዶች የመንገዳቸውን አቅጣጫ በመሳት በበረሓ ተንከራተቱ፤ ሊኖሩ ወደሚችሉበት ከተማ የሚመራቸውን መንገድ ለማግኘት አልቻሉም። |
በደመናና በጭጋግ ቀን እረኛ ከበጎቹ መካከል የተለየውን እንደሚፈልግ፥ እንደዚሁ በጎችን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በጭጋግ ቀን ከተበተኑባቸው ሀገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ።
በጎች በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ በጎችም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ የሚፈልግም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም።
ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅበዘበዛሉ፤ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ግልሙትናችሁን ይሸከማሉ።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ በጠና ተቈጣ። በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ያደረገ ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ውስጥ አንከራተታቸው።
በምድረ በዳ አጠገባቸው፤ በጥማትና በድካም ቦታ፥ በውድማ ከበባቸው፤ መገባቸው፤ መራቸውም፤ እንደ ዐይን ብሌንም ጠበቃቸው።
የሚናደፍ እባብና ጊንጥ፥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት፥ በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከጭንጫ ድንጋይም ጣፋጭ ውኃን ያወጣልህን፥