አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
መዝሙር 103:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጨረቃን በጊዜው ፈጠርህ፤ ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቷል፤ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው፤ የእርሱም ገዢነት በሁሉም ላይ ነው። |
አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፤ አቤቱ፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ የሥልጣን ሁሉ ጌታ ነህ፤ ኀይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ኀያል ነህ፤ ታላቅ ለማድረግ፥ ለሁሉም ኀይልን ለመስጠት ዓለምን ሁሉ በእጅህ የያዝህ ነህ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው?