እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
መዝሙር 103:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እህልን ከምድር ያወጣ ዘንድ፥ ለምለሙን ለሰው ልጆች አገልግሎት፥ ሣርንም ለእንስሳ ያበቅላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ ትቢያ መሆናችንንም ያስባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን ያስታውሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከምን እንደ ተፈጠርን ያውቃል፤ ዐፈር መሆናችንንም ያስታውሳል። |
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና።”
ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።”
አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ በሥጋም በነበረበት ጊዜ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይሰጥ ፈጣሪህን አስብ።
ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን፥ “አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ የተደረገ አድራጊውን፥ “በማስተዋል አላሳመርኸኝም” ይለዋልን?