የዱር አራዊትን ሁሉ ያጠጣሉ፥ የበረሃ አህዮችም ጥማታቸውን ያረካሉ።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ።
ሰማይ ከምድር ከፍ የሚለውን ያኽል እግዚአብሔር ለሚፈሩት የሚሰጠው ፍቅር ታላቅ ነው።
“ልዑል የወደደውን ያደርግ ዘንድ የሚገባው አይደለምን? ትዕቢተኞችንስ አያዋርዳቸውምን?
በዚያም ዎፎች ይዋለዳሉ፥ የሸመላ ቤትም ይጐራበታቸዋል።
ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም እንደ ሆነ፥ የእስራኤል ወገን ንገሩ።
መንገድህን ለአግዚአብሔር ግለጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።
ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፤ በኀጢአተኛው ደምም እጁን ይታጠባል።
ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።
ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ፥ ዐሳቤም ከዐሳባችሁ የራቀ ነው።
ይቅርታውም ለሚፈሩት ለልጅ ልጅ ነው።