ምንጮችን ወደ ቆላዎች የሚልክ፤ በተራሮች መካከል ውኆች ያልፋሉ፤
እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።
እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።
በኃጢአታችን መጠን አልቀጣንም፤ በበደላችንም ልክ አልከፈለንም።
ስለ ክፉ ሥራችንና ስለ ታላቁ በደላችን ካገኘን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አምላካችን እንደ ኀጢአታችን ብዛት አልቀሠፍኸንም፤ ነገር ግን ድኅነትን ሰጠኸን።
ነገር ግን አንተ ኀያል፥ ቸርና መሓሪ አምላክ ነህና በምሕረትህ ብዛት ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፤ አልተውሃቸውምም።
የጥበቡን ኀይል ቢገልጥልህ! ባንተ ላይ ያለው እጥፍ ነውና። ያንጊዜም ከእግዚአብሔር ዘንድ በበደልህ ያገኘህ ትክክል እንደ ሆነ ታውቃለህ።
ያንጊዜም ሰው ራሱን ይነቅፋል፤ እንዲህም ይላል፦ ‘እኔ ምን አድርጌአለሁ? እንደ ኀጢአቶችም መጠን አልቀጣኝም፤
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመናል።
ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።
አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፣ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፣ በዓመታት መካከል ትታወቅ፣ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።