ምሳሌ 7:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ አንገቱን ደፍቶ ይከተላታል፥ ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፥ ወደ እስራት እንደሚሄድ ውሻ፥ ሆዱ እንደ ተወጋ ዋሊያ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዕርድ እንደሚነዳ በሬ፣ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ አጋዘን፣ ሳያንገራግር ተከተላት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ እንዲህ ስቶ ይከተላታል፥ በሬ ለመታረድ እንደሚነዳ፥ አጋዘን ቸኩሎ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሬ ወደሚታረድበት ስፍራ እንደሚነዳ፥ አጋዘንም ቸኲሎ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ፥ ወዲያውኑ እርስዋን ተከትሎ ሄደ፤ |
ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን ገረፈው፤ በእግዚአብሔርም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው አዘቅት ውስጥ ጣለው።
በከተማውም ፊት ለፊት ቤተ መቅደስ ያለው የድያ ካህን ኮርማዎችንና የአበባ አክሊሎችን ወደ ደጃፍ አመጣ፤ ከሕዝቡም ጋር ሆኖ ሊሠዋላቸው ወደደ።