እንዲህም ሆነ፤ ዓይበታቸውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእነርሱ እያንዳንዳቸው ብራቸውን በዓይበታቸው ተቋጥሮ አገኙት፤ እነርሱም አባታቸውም የተቋጠረ ብራቸውን አይተው ፈሩ።
ምሳሌ 7:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእጁም የወርቅ ከረጢት ይዞአል፤ ወደ ቤቱ ቢመለስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገንዘብ የተሞላ ቦርሳ ወስዷል፤ ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን አይመለስም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእጁም የብር ከረጢት ወስዶአል፥ ሙሉ ጨረቃ በሆነች ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለሳል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ገንዘብ ይዞ ስለ ሄደ እስከ ሁለት ሳምንት አይመለስም።” |
እንዲህም ሆነ፤ ዓይበታቸውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእነርሱ እያንዳንዳቸው ብራቸውን በዓይበታቸው ተቋጥሮ አገኙት፤ እነርሱም አባታቸውም የተቋጠረ ብራቸውን አይተው ፈሩ።
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ለማጠን፥ የገጹንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በአምላካችንም በእግዚአብሔር በዓላት ለማቅረብ እኔ ልጁ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራለሁ፤ እርሱንም እቀድሳለሁ።