አብርሃምም ሚስቱን ሣራን “እኅቴ ናት” አላቸው፤ የከተማዪቱ ሰዎች ስለ እርስዋ እንዳይገድሉት “ሚስቴ” ናት ማለትን ፈርቶአልና፤ የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት።
ምሳሌ 6:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ጐልማሳ ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፤ የሚነካትም ሁሉ አይነጻም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰው ሚስት ጋራ የሚተኛም እንደዚሁ ነው፤ የሚደርስባትም ከቅጣት አያመልጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሰው ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፥ የሚነካትም ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ግንኙነት የሚያደርግ እንደዚሁ ነው፤ የሌላውን ሰው ሚስት የሚነካ ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም። |
አብርሃምም ሚስቱን ሣራን “እኅቴ ናት” አላቸው፤ የከተማዪቱ ሰዎች ስለ እርስዋ እንዳይገድሉት “ሚስቴ” ናት ማለትን ፈርቶአልና፤ የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት።
የልቅሶዋም ወራት ሲፈጸም ዳዊት ልኮ ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስትም ሆነችው፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሆነ።
አኪጦፌልም አቤሴሎምን፥ “ቤት ሊጠብቁ ወደ ተዋቸው ወደ አባትህ ቁባቶች ግባ፤ እስራኤልም ሁሉ አባትህን እንዳሳፈርኸው ይሰማሉ፤ ከአንተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃቸው ይበረታል” አለው።
“የባልንጀራህን ሚስት፥ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ እርሻውንም፥ ሎሌውንም፥ ገረዱንም፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከብቱንም ሁሉ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማንኛውንም አትመኝ።”
በተራራም ላይ ባይበላ፥ ዐይኖቹንም ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ፥ የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ፥ አደፍም ወዳለባት ሴት ባይቀርብ፤
ሰውም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ሰሰነ፤ አባትም የልጁን ሚስት በኀጢአት አረከሰ፤ በአንቺም ዘንድ ወንድም የአባቱን ልጅ እኅቱን አስነወረ።
ሰይፋችሁን ይዛችሁ ቆማችኋል፤ ርኩስ ነገርን ታደርጋላችሁ፤ የባልንጀሮቻችሁንም ሚስቶች ታስነውራላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን? ስለዚህም እንዲህ በላቸው፦
“ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራዪቱ ፈጽመው ይገደሉ።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።