ምሳሌ 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውነትህ በደከመ ጊዜ፥ ኋላ ትጸጸታለህ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዕድሜህ መጨረሻ ታቃሥታለህ፤ ሥጋህና ሰውነትህ ሲከዳህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለንተናህ ተበልቶ ከማለቁ የተነሣ በሞት ጣዕር ተይዘሃል፥ |
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
ውኃውን ካጠጣት በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ራስዋን አርክሳና ባልዋን ቸል ብላው ከሆነ፤ የመርገሙ መራራ ውኃ ወደ ሆድዋ ይገባል፤ ሆድዋንም ይሰነጥቀዋል፤ ጎኗም ይረግፋል፤ ሴቲቱም በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች።
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”