ምሳሌ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ ጥበቤን ተመልከት፤ ጆሮህም ወደ ቃሌ ያድምጥ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ፤ ጥበቤን ልብ በል፤ የማስተዋል ቃሌንም በጥሞና አድምጥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጄ ሆይ፥ ጥበቤን አድምጥ፥ ጆሮህን ወደ ትምህርቴ አዘንብል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጄ ሆይ! እኔ ወደምነግርህ ጥበብና ማስተዋል አተኲረህ አድምጥ። |
በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።