ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
ምሳሌ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያስተምሩኝም ነበር፥ እንዲህም ይሉኝ ነበር፦ ቃላችን በልብህ ይኑር፤ ትእዛዞቻችንንም ጠብቅ፥ አትርሳቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፤ “ቃሌን በሙሉ በልብህ ያዝ፤ ትእዛዜንም ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያስተምረኝም ነበር እንዲህም ይለኝ ነበር፦ “ልብህ ቃሌን በጥብቅ ይያዘው፥ ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቴም እንዲህ እያለ ያስተምረኝ ነበር፤ “ቃሌን በሙሉ ልብህ ያዘው፤ ትእዛዞቼንም ፈጽም፤ በሕይወትም ትኖራለህ። |
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አክብረው ትጸናለህም። ከእርሱ በቀር ሌላውን አትፍራ፥ ከእርሱ በቀር የሚገድልህም የሚያድንህም የለምና። ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፤ ቃሌንም እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ፤
ስሙኝ፤ ጎዳናዬን ተከተሉ፤ አድምጡኝም፤ ሰውነታችሁም በበረከት ትኖራለች፤ የታመነችዪቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
ኤርምያስም እንዲህ አለው፥ “አሳልፈው አይሰጡህም። እኔ የምነግርህን የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ ለአንተም ይሻልሃል፤ ነፍስህም በሕይወት ትኖራለች።
“ለራስህ ዕወቅ፤ ሰውነትህን ፈጽመህ ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ይህን ሁሉ ነገር አትርሳ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ከልቡናህ አይውጣ፤ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህም አስተምራቸው።
በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፤ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ።