ምሳሌ 4:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኀጢአት መብልን ይበላሉ፥ በግፍ የወይን ጠጅም ይሰክራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤ የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክፋትን እንጀራ ይበላሉና፥ የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐመፅና ግፍ ለእነርሱ እንደ መብልና እንደ መጠጥ ናቸው። |
ክፉውን መልካም መልካሙንም ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!
ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ በጠማማነት ይሄዳልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፤ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።
እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።