Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 4:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዐመፅና ግፍ ለእነርሱ እንደ መብልና እንደ መጠጥ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤ የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የክፋትን እንጀራ ይበላሉና፥ የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የኀጢአት መብልን ይበላሉ፥ በግፍ የወይን ጠጅም ይሰክራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 4:17
17 Referencias Cruzadas  

“እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።


ደጋግ ሰዎች የመልካም አነጋገራቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ የአታላዮች ምኞት ግን የግፍ ሥራ ለመፈጸም ነው።


በማጭበርበር የምታገኘው ነገር እንደ ጣፋጭ ምግብ ሊያስደስትህ ይችላል፤ ነገር ግን ውሎ ሲያድር በአፍ ውስጥ እንደ አሸዋ ይሆናል።


“ሰርቀው የሚጠጡት ውሃ ይጣፍጣል፤ ተሸሽገው የሚበሉትም እንጀራ ያስደስታል።”


በማታለል ገመድ ኃጢአትን፥ በሠረገላ ገመድ ተንኰልን ለሚጐትቱ ወዮላቸው!


ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑን ጨለማ ለሚያስመስሉ፥ ጣፋጩን መራራ፥ መራራውን ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!


እያንዳንዱ ከባልንጀራው ተንኰል ይጠንቀቅ፤ ወንድሙን እንኳ ቢሆን ማመን የለበትም፤ ወንድም የተባለ ሁሉ (እንደ ያዕቆብ) አታላይ ሆኖአል፤ ወዳጅ የተባለም ሁሉ የባልንጀራውን ስም ያጠፋል።


እግዚአብሔር ስለ ሐሰተኞች ነቢያት እንዲህ ይላል፦ “ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን ‘ሰላም ይወርድላችኋል’ እያሉ ይሰብካሉ፤ ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ‘ጦርነት ይመጣባችኋል’ እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፤


ሀብታሞቻችሁ በግፍ የተሞሉ ናቸው፤ የከተማይቱ ነዋሪዎችም ሐሰትን ይናገራሉ፤ በአንደበቶቻቸውም ይሸነግላሉ።


እጆቻቸው ክፉ ነገርን ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ባለ ሥልጣኑና ዳኛው ጉቦ ይጠይቃሉ፤ ኀይለኛ ፍላጎቱን በግዴታ ተግባራዊ ያስደርጋል፤ በዚህም ዐይነት ሁሉም ፍርድን ያጣምማሉ።


መሪዎችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ዳኞችዋም ለነገ ሳያስተርፉ ያገኙትን ሁሉ በልተው እንደሚጨርሱ እንደ ተራቡ የማታ ተኲላዎች ናቸው።


“ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገባ፥ በሩን የምትዘጉ እናንተ ግብዞች፥ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ!” [


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos