በተጓዙበትም ቦታ አትሂድ፤ ከእነርሱ ፈቀቅ በል ተመለስም።
ከዚያ አትድረስ፤ አትጓዝበት፤ ሽሸው፤ መንገድህን ይዘህ ሂድ፤
ከእርሷ ራቅ፥ አትሂድባትም፥ ራቅ በል ተዋትም።
ከእርሱ ራቅ፤ በዚያም አትራመድ፤ ከእርሱ ርቀህ በራስህ መንገድ ሂድ።
በእጆችህ በደል ቢኖር ካንተ አርቀው፤ በልብህም ኀጢአት አይኑር፤
ብትመለስ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራስህን ብታዋርድ፥ ኀጢአትንም ከልብህ ብታርቅ፥
ከዐመፅ ፍርድ ሁሉ ራቅ፤ በደል የሌለበትንና ጻድቅን አትግደል፤ ኀጢአተኛውንም በመማለጃ አታድን፤
ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ፤
ልጄ ሆይ፥ በክፉ ሰዎች አትቅና፥ ከእነርሱም ጋር መኖርን አትውደድ፤
በክፉዎች መንገድ አትሂድ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትቅና።
ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም።
መንገድህን ከእርስዋ አርቅ፥ ወደ ቤቷም ደጅ አትቅረብ፥
እንደ ሚዳቋ ከወጥመድ፥ እንደ ወፍም ከጭራ ወጥመድ ትድን ዘንድ።
በጽድቅ የሚሄድ፥ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በደልንና ኀጢአትን የሚጠላ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚደፍን፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።
የሥራ ፍሬ ከሌላቸው፥ ሁለንተናቸውም ጨለማ ከሆነ ሰዎች ጋር አትተባበሩ፤ ገሥጹአቸው እንጂ።
ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።