ምሳሌ 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላሟልነትን ታገኛለህና፥ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መልካምን ዐስብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ሞገስንና ማስተዋልን፣ በእግዚአብሔርና በሰው ዘንድ ታገኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ብታደርግ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መወደድንና መልካም ዝናን ታገኛለህ። |
እግዚአብሔርንም ያመሰግኑ ነበር፤ በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ መወደድ ነበራቸው፤ እግዚአብሔርም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።
እግዚአብሔርም ሐናን ጐበኘ፤ ዳግመኛም ፀነሰች፥ ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችን ወለደች። ብላቴናው ሳሙኤልም በእግዚአብሔር ፊት አደገ።