ነፍስህ ትድን ዘንድ፥ ለአንገትህም ሞገስ ይሆንህ ዘንድ። ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።
ለነፍስህ ሕይወት፣ ለዐንገትህም ጌጥ ይሆናሉ።
ለነፍስህም ሕይወት ይሆናሉ፥ ለአንገትህም ሞገስ።
እነርሱም ለአንተ ረጅምና የአማረ ሕይወትን ይሰጡሃል።
ለራስህ የክብር ዘውድን ለአንገትህም የወርቅ ድሪ ታገኛለህና።
በጎ ዐሳብ ገንዘብ ላደረጋት ሰው የሕይወት ምንጭ ናት፤ የሰነፎች ትምህርት ግን ክፉ ናት።
ጥበብን የሚያገኝ ራሱን ይወድዳል፥ ማስተዋልንም የሚጠብቅ መልካም ነገርን ያገኛል።
ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ክብርን ያገኛል።
ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤ ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና።
ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ናቸውና።
መንገዶቼ የሕይወት መንገዶች ናቸውና። እኔን ያገኘ ሕይወትን አገኘ፤ ፈቃዱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይዘጋጃል።
ጌታ ሆይ፥ ስለ እርስዋ እንዲህ አልሁህ፤ ነፍሴን አዳንሃት፤ ደስ አለኝ፤ በሕይወትም ኖርሁ።
ይህ ነገር ሕይወታችሁ ነው እንጂ ለእናንተ ከንቱ አይደለምና፤ በዚህም ነገር ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር ዘመናችሁ ይረዝማል።”