አባትህም ዳዊት እንደ ሄደ፥ ሥርዐቴንና ትእዛዜን ትጠብቅ ዘንድ በመንገዴ የሄድህ እንደ ሆነ፥ ዘመንህን አበዛልሀለሁ።”
ምሳሌ 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ዘመናትንና ረጅም ዕድሜን ሰላምንም ይጨምሩልሃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤ ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ቀኖች፥ የሕይወት ዓመታትና ሰላምም ይጨምሩልሃልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔ ትምህርት ረጅም ዕድሜን ከብዙ ተድላና ደስታ ጋር ይሰጥሃል። |
አባትህም ዳዊት እንደ ሄደ፥ ሥርዐቴንና ትእዛዜን ትጠብቅ ዘንድ በመንገዴ የሄድህ እንደ ሆነ፥ ዘመንህን አበዛልሀለሁ።”
በወራቱ የደረሰ አዝመራ እንዲሰበሰብ፥ የእህሉ ነዶም በወቅቱ ወደ አውድማ እንዲገባ፥ በረዥም ዕድሜ ወደ መቃብር ትገባለህ።
የተስፋ አምላክ እግዚአብሔርም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በተስፋ ያበዛችሁ ዘንድ በእምነት ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይፈጽምላችሁ።
በምድር ላይ የሰማይን ዘመን ያህል ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር ዘመናችሁ የልጆቻችሁም ዘመን ይረዝም ዘንድ፤
ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።