መንገዶችዋ መልካም መንገዶች ናቸው። ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።
መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ ጐዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።
መንገድዋ የደስታ መንገድ ነው፥ ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።
መንገዶችዋ የደስታ መንገዶች ናቸው፤ መተላለፊያዎችዋም ሁሉ ሰላም የሰፈነባቸው ናቸው።
የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ።
በእጃቸው ተንኮል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃን ተሞልታለች።
ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ባላጋራ ሆኑኝ፥ ከበውም ደበደቡኝ፥ ዘመዶቼም ተስፋ ቈርጠው ተለዩኝ።
ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።
ጥበብ ወደ ልብህ በመጣች ጊዜ፥ ዕውቀትም ለነፍስህ መልካምና ክብር በሆነች ጊዜ፥
እነርሱን በልብህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህ በአንድነት ደስ ያሰኙሃል።
በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ የምትደገፍ ነፍስን ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
በሩቅም በቅርብም ላሉ በሰላም ላይ ሰላም ይሁን፤ እፈውሳቸውማለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
በጨለማና በሞት ጥላ ለነበሩት ብርሃኑን ያሳያቸው ዘንድ፥ እግሮቻችንንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ።”
እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን፥ በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እናገናለን።