La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 24:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የነገሩትን የሚጠብቅ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የሚቀበልም እርሱን ይቀበለዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህም ደግሞ የጠቢባን ምሳሌዎች ናቸው፦ በዳኝነት አድልዎ ማድረግ ተገቢ አይደለም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነዚህ ደግሞ የጠቢባን ቃሎች ናቸው። በፍርድ ላይ ማዳለት መልካም አይደለም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የጥበበኞች ተጨማሪ አባባሎች፦ በዳኝነት ማዳላት ስሕተት ነው፤

Ver Capítulo



ምሳሌ 24:23
18 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ላይ ይሁን፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በደ​ልና ለሰው ፊት ማድ​ላት፥ መማ​ለ​ጃም መው​ሰድ የለ​ምና ሁሉን ተጠ​ን​ቅ​ቃ​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ከእ​ርሱ ወደ ኋላ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ች​ሁን? እስኪ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቈቅልሾችን ያውቃል።


የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥


ለመስማት ጆሮህን ወደ ጠቢባን ቃል አዘንብል፥ የእኔንም ቃል ስማ፥ መልካምንም ታውቅ ዘንድ ልብህን አቅርብ።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ድን ነው? እኔ አደ​ከ​ም​ሁት፤ አጸ​ና​ሁ​ትም፤ እኔ እንደ ተወ​ደደ አበባ አፈ​ራ​ዋ​ለሁ፤ ፍሬ​ህም በእኔ ዘንድ ይገ​ኛል።


“በፍ​ርድ ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ፤ ለድሃ አታ​ድላ፤ ባለ​ጠ​ጋ​ው​ንም አታ​ክ​ብር፤ ነገር ግን ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ በእ​ው​ነት ፍረድ።


የእ​ው​ነት ፍርድ ፍረዱ እንጂ ለሰው ፊት በማ​ድ​ላት አት​ፍ​ረዱ።”


በፍ​ር​ድም ፊት አትዩ፤ ለት​ል​ቁም፥ ለት​ን​ሹም በእ​ው​ነት ፍረዱ፤ ለሰው ፊት አታ​ድሉ፤ ፍርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። አንድ ነገር ቢከ​ብ​ዳ​ችሁ እር​ሱን ወደ እኔ አም​ጡት፤ እኔም እሰ​ማ​ዋ​ለሁ፤


ፍር​ድን አታ​ጣ​ምም፤ ፊት አይ​ተ​ህም አታ​ድላ፤ ጉቦን አት​ቀ​በል፥ ጉቦ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ቃል ያጣ​ም​ማ​ልና ጉቦ አት​ቀ​በል።


ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።