ምሳሌ 24:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ ከእነርሱ ለአንዱ ስንኳ እንቢ አትበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ፤ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፤ ከዐመፀኞችም ጋራ አትተባበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጄ ሆይ፥ ጌታንና ንጉሥን ፍራ፥ ከዓመፀኞችም ጋር አትደባለቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጄ ሆይ! እግዚአብሔርን ፍራ ንጉሥንም አክብር፤ በእነርሱም ላይ ከሚያምፁ ሰዎች ጋር አትተባበር። |
እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ፥ “በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን የራስህን ቤት ተመልከት” ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደየቤታቸው ተመለሱ።
እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርም አመኑ፤ ባሪያውንም ሙሴን አከበሩ።
ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው።