ምሳሌ 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከስስታም ሰው ጋር አትመገብ፥ ምግቡንም አትመኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሥሥታምን ምግብ አትብላ፤ ጣፋጭ መብሉም አያስጐምጅህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንፉግን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የስስታምን እንጀራ አትብላ፤ የሚያቀርብልህም ጥሩ ምግብ አያስጐምጅህ፤ |
ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል።
ሰባተኛው ዓመት የምሕረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አልሰጠውምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በልብህ እንዳታስብ ለራስህ ዕወቅ። ወንድምህም ዐይኑን በአንተ ላይ ያከፋል፤ እርሱም ወደ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ይጮሃል፤ ኀጢአትም ይሆንብሃል።
በአንተ ዘንድ የተለሳለሰችና የተቀማጠለች፥ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ የእግር ጫማዋን በምድር ላይ ያላደረገችው ሴት፥ አቅፋ በተኛችው ባልዋ፥ በወንድና በሴት ልጅዋም ትቀናለች፥