በእጅህ ተቀበል፥ እንደዚህም ታዘጋጅ ዘንድ እንዳለህ ዕወቅ።
ሆዳም ብትሆን እንኳ፣ በጕረሮህ ላይ ካራ አጋድምበት፤
ሰውነትህም ቢጎመጅ፥ በጉሮሮህ ላይ ካራ አድርግ።
ለመብላት ብትጓጓ እንኳ ብዙ ከመብላት ተቈጠብ።
ሄዶም አመጣ፤ ለእናቱም ሰጣት፤ እናቱም መብልን አባቱ እንደሚወድደው አደረገች።
በመኳንንት ማዕድ ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ ያቀረቡልህን ፈጽመህ ዕወቅ፤
የወይን ጠጅ ጠጭ አትሁን፤ ለሥጋም አትሳሳ
ነገር ግን ለሌላ ሳስተምር፥ እኔ ለራሴ የተናቅሁ እንዳልሆን ሰውነቴን አስጨንቃታለሁ፥ ሥጋዬንም አስገዛዋለሁ።
እነዚህም ፍጻሜያቸው ለጥፋት የሆነ፥ ሆዳቸውን የሚያመልኩ፥ ክብራቸውም ውርደት የሆነባቸው፥ ምድራዊዉንም የሚያስቡ ናቸው።