አንተ በበትር ትመታቸዋለህ፥ ነፍሳቸውን ግን ከሞት ታድናለህ።
በአርጩሜ ቅጣው፤ ነፍሱንም ከሞት አድናት።
በበትር ትመታዋለህ፥ ነፍሱንም ታድናለህ።
እንዲያውም በአርጩሜ ብትመታው ሕይወቱን ከሞት ለማዳን ጥሩ ዋስትና ይሆነዋል።
በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ ልጁን የሚወድድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።
አለማወቅ የጐልማሳን ልብ ከፍ ከፍ አደረገች፤ በትርና ተግሣጽ ከእርሱ ርቀዋልና።
ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኰነን በጌታ እንገሠጻለን።
ሥጋውን ጎድቶ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን ነፍሱ ትድን ዘንድ እንዲህ ያለውን ሰው ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት።