ከነቢያትም ልጆች የአንዱ ሚስት የሆነች አንዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
ምሳሌ 22:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሆች ባለጠጎችን ይገዛሉ፥ አገልጋዮችም ለጌቶቻቸው ያበድራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለጠጋ ድኻን ይገዛል፤ ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብታም ድሆችን ይገዛል፥ ተበዳሪም የአበዳሪ ጥገኛ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድኻ የሀብታም ሰው አገልጋይ ነው፤ ገንዘብ የሚበደር የአበዳሪው ባሪያ ነው። |
ከነቢያትም ልጆች የአንዱ ሚስት የሆነች አንዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
ሕዝቡ እንደ ካህኑ፥ ባሪያውም እንደ ጌታው ባሪያይቱም እንደ እመቤቷ፥ የሚሸጠውም እንደሚገዛው፥ ተበዳሪውም እንደ አበዳሪው፥ ዕዳ ከፋዩም እንደ ዕዳ አስከፋዩ ይሆናል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ጻድቁን በብር፥ ችጋረኛውንም ምድርን በሚረግጡበት አንድ ጥንድ ጫማ ሸጠውታልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የእስራኤል ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኞችንም የምታስጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።
ድሃውን በብር፥ ችግረኛውንም በአንድ ጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ፥ በእህላችንም ንግድ እንድንጠቀም ሰንበት መቼ ያልፋል? የምትሉ እናንተ ሆይ! ይህን ስሙ።”