ምሳሌ 21:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ሰው ሲዋረድ የዋህ ሰው ዐዋቂ ይሆናል፤ ጥበብን የሚረዳ ሰውም ዕውቀትን ይቀበላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፌዘኛ ሲቀጣ፣ አላዋቂ ጥበብን ያተርፋል፤ ጠቢብ ሰው ቢማር ዕውቀትን ያገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፌዘኛ ቅጣትን በተቀበለ ጊዜ አላዋቂ ሰው ጥበብን ያገኛል፥ ጠቢብም ቢማር እውቀትን ይቀበላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፌዘኛ በሚቀጣበት ጊዜ አላዋቂ ሰው ጥበብን ያገኛል፤ ለብልኅም ሰው ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ የበለጠ ዐዋቂ ይሆናል። |
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።
በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።