ምሳሌ 20:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ከገንዘቡ በችኮላ የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ይሆንበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በችኰላ ስእለት መሳል፣ ከተሳሉም በኋላ ማቅማማት ለሰው ወጥመድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው በችኰላ፦ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኋላ እንዳትጸጸት ለእግዚአብሔር ከመሳልህ በፊት ተጠንቅቀህ አስብ። |
እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኩል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ይሁን።
“ሰው ቢዘነጋ፥ ሳያውቅም ለእግዚአብሔር በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኀጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ከመንጋዉ ነውር የሌለበትን እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተገመተውን አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት ያቀርባል።
በአፍህ የተናገርኸውን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በፈቃድህ ተስለሃልና ከከንፈርህ የወጣውን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።
“ወደ ባልንጀራህ እርሻ በገባህ ጊዜ እሸቱን በእጅህ ቀጥፈህ ብላ፤ ወዳልታጨደው ወደ ባልንጀራህ እህል ግን ማጭድ አታግባ።
አባቶቻቸውና ወንድሞቻቸውም ሊጣሉአችሁ ወደ እኛ በመጡ ጊዜ፦ ስለ እኛ ማሩአቸው፥ እኛ ሚስት ለያንዳንዳቸው በሰልፍ አልወሰድንላቸውምና፥ እናንተም በደል ይሆንባችሁ ስለ ነበር አላጋባችኋቸውምና፥” እንላቸዋለን።