ምሳሌ 20:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዳትወገድ ማማትን አትውደድ። ድሃም እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ ዐይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንቅልፍ አትውደድ፤ አለዚያ ድኻ ትሆናለህ፤ ዐይንህን ክፈት፤ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖርሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፥ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጊዜህን በእንቅልፍ ብትጨርስ ትደኸያለህ፤ ተግተህ ብትሠራ ግን በቂ ምግብ ይኖርሃል። |
ምድሩን የሚያርሳት ሰው እንጀራን ይጠግባል፤ ቦዘኔነትን የሚከተል ግን የአእምሮ ድህነትን ይሰበስባል። በወይን ግብዣ ራሱን ደስ የሚያሰኝ ሰው በሰውነቱ ውርደትን ያመጣል።
የመርከቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ” አለው።