ዘወርም ብሎ አያቸው፤ በእግዚአብሔርም ስም ረገማቸው፤ ወዲያውም ከዱር ሁለት ድቦች ወጥተው ከእነርሱ አርባ ሁለቱን ሰባበሩአቸው።
ምሳሌ 19:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለክፉዎች ሰዎች መቅሠፍት ተዘጋጅቶላቸዋል፥ ለሰነፎችም እንደዚሁ ቅጣት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለፌዘኞች ቅጣት፣ ለሞኞችም ጀርባ ጅራፍ ተዘጋጅቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሚያፌዙ ሰዎች ፍርድ ተዘጋጅታለች፥ ለሰነፎችም ጀርባ በትር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለፌዘኞች ፍርድ፥ ለሞኞችም ግርፋት ተዘጋጅቶላቸዋል። |
ዘወርም ብሎ አያቸው፤ በእግዚአብሔርም ስም ረገማቸው፤ ወዲያውም ከዱር ሁለት ድቦች ወጥተው ከእነርሱ አርባ ሁለቱን ሰባበሩአቸው።
ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤
ልጄ ሆይ፥ ለራስህ ጠቢብ ብትሆን ለባልንጀራህም ጠቢብ ትሆናለህ፥ ክፉም ብትሆን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚያዘጋጅ ሰው ይመስላል። እርሱም የሚበርር ዎፍን እንደሚከተል ነው። የወይኑ ቦታ መንገዱን ተወ፤ የሚሰማራባትን መንገድ ዘነጋ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች ምድርም ይሄዳል፤ የማያፈራና የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።
አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚያደርገውን ያለቀና የተቈረጠ ነገርን ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራታችሁ እንዳይጸናባችሁ እናንተ ደስ አይበላችሁ።
በደለኛውም መገረፍ ቢገባው እንዲገረፍ ፈራጁ በፊቱ በምድር ላይ ያጋድመው፤ የግርፋቱም ቍጥር እንደ ኀጢአቱ መጠን ይሁን።
እግዚአብሔር የሚወደውን ይገሥጻልና፥ የሚወደደውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል” ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል።