ምሳሌ 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድሃ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ያነሣሣዋል፥ በሚጠፋም ላይ ደስ የሚለው ከፍርድ አይነጻም፥ የሚራራ ግን ምሕረትን ያገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድኾች የሚያፌዝ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ በሌላው ሰው መከራ ደስ የሚለው ከቅጣት አያመልጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድሀ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ይሰድባል፥ በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድኾች ብታፌዝ የፈጠራቸውን እግዚአብሔርን እንደ ሰደብክ ይቈጠራል፤ በሌላው ሰው ላይ በሚደርሰው መከራ ብትደሰት አንተም ትቀጣለህ። |
እኔም አንተን ተከትዬ አልደከምሁም፥ የሰውንም ቀን አልተመኘሁም፤ አንተ ታውቃለህ፤ ከከንፈሬ የወጣውም በፊትህ ነው።
ለአሞንም ልጆች እንዲህ በል፦ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት በተማረኩ ጊዜ ስለ እነርሱ ደስ ብሎሃልና፤
በቅዱሱ ተራራዬ ላይ እንደ ጠጣህ እንዲሁ አሕዛብ ሁሉ ወይንን ይጠጣሉ፤ አዎን፥ ይጠጣሉ፥ ይጨልጡማል፤ እንዳልነበሩም ይሆናሉ።
ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?