ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
ምሳሌ 17:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰነፍ ልብ ገንዘብ ላደረጋት ኀዘን ናት፥ አባት ባልተማረ ልጁ ደስ አይለውም፥ ብልህ ልጅ ግን እናቱን ደስ ያሰኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ ልጅ መውለድ ሐዘን ያስከትላል፤ የተላላም አባት ደስታ የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰነፍን የሚወልድ ኀዘን ይሆንበታል፥ የደንቆሮ ልጅም አባት ደስ አይለውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰነፍ ልጅ አባት ከሐዘንና ከብስጭት በቀር ምንም ደስታ የለውም። |
ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፤ በበሩም ላይ ወዳለችው ሰገነት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ በአንተ ፋንታ እኔ እንድሞት ቤዛህም እንድሆን ማን ባደረገኝ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።
የእኔ ደስታ የሁላችሁ እንደ ሆነ በሁላችሁ አምኛለሁና በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ ከሚገባቸው ኀዘን እንዳያገኘኝ ይህን ጻፍሁላችሁ።