ምሳሌ 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትዕቢት ጥፋትን፣ የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዕቢት ጥፋትን፥ ኩሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢት ወደ ጥፋት ይወስዳል፤ ትምክሕተኛነትም ወደ ውድቀት ያደርሳል። |
በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ወደ አራራትም ሀገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ድፍረትህና የልብህ ኵራት አነሣሥተውሃል። ቤትህንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
አንቺ ትዕቢተኛ ሆይ!፥ ትደክሚያለሽ፤ ትወድቂያለሽም፤ የሚያነሳሽም የለም፤ በዛፎችሽ ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያሽ ያለውንም ሁሉ ትበላለች።”
በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ፤ ያዩህም፥ ይዘብቱብህም ዘንድ በነገሥታት ፊት አሳልፌ ሰጠሁህ።
የግብፅም ምድር ባድማና ውድማ ትሆናለች፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ አንተ፦ ወንዙ የእኔ ነው፤ የሠራሁትም እኔ ነኝ ብለሃልና።
በኋላ ያ አንተንም እርሱንም የጠራ መጥቶ፦ ይህን ቦታ ለእርሱ ተውለት ይልሃልና፤ ያንጊዜም አፍረህ ትመለሳለህ፤ ወደ ዝቅተኛ ቦታም ትወርዳለህ።