ምሳሌ 16:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሥ ቍጣ እንደ መልአከ ሞት ነው፤ ብልህ ሰው ግን ያቈላምጠዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ቍጣ የሞት መልእክተኛ ነው፤ ጠቢብ ሰው ግን ቍጣውን ያበርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሥ ቁጣ እንደ ሞት መልእክተኛ ነው፥ ጠቢብ ሰው ግን ያቈላምጠዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው። ብልኅ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል። |
ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን የሆነውን ስንኳ ያጠፋል። ትዕግሥተኛ ሰው ክርክርን ያጠፋል፥ ኀጢአተኛ ሰው ግን ጠብን ፈጽሞ ያነሣል።
ሄሮድስም በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ተቈጥቶ ነበር፤ በአንድነትም ወደ እርሱ መጥተው የንጉሡን ቢትወደድ በላስጦስን እንዲያስታርቃቸው ማለዱት፤ የሀገራቸው ምግብ ከንጉሥ ሄርድስ ነበርና።
እኛስ በክርስቶስ አምሳል እንለምናለን፤ እግዚአብሔርም በእኛ መጽናናትን ይሰጣችኋል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ትታረቁ ዘንድ በክርስቶስ እንለምናችኋለን።