ምሳሌ 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተሻለ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል። ዐመፀኛ ሰው ግን ቸል ይባላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያገኛል፤ ተንኰለኛውን ግን እግዚአብሔር ይፈርድበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ሰው ከጌታ ዘንድ ሞገስን ያገኛል፥ ተንኰለኛውን ሰው ግን ጌታ ይፈርድበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግ ሰው ከእግዚአብሔር ሞገስን ያገኛል፤ ክፉ ሐሳብ ያላቸውን ሰዎች ግን እርሱ ይፈርድባቸዋል። |
ስሕተተኞች ክፉን ያስባሉ፤ ደጋጎች ግን ምሕረትንና እውነትን ያስባሉ። ክፋትንም የሚሠሩ ምሕረትንና ይቅርታን አያውቁም። ነገር ግን ታማኝነትና ቸርነት ደግ በሚሠሩ ዘንድ ናቸው።
መንፈስን ለማስቀረት በመንፈሱ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞትም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በጦርነትም ጊዜ ስንብት የለም፥ ኀጢአትም ሠሪውን አያድነውም።