ጻድቃን ለዘለዓለም አይናወጡም፤ ኃጥኣን ግን በምድር ላይ አይቀመጡም።
ጻድቃን ፈጽሞ አይነቀሉም፤ ክፉዎች ግን በምድር አይኖሩም።
ጻድቅ ለዘለዓለም አይናወጥም፥ ክፉዎች ግን በምድር ላይ አይቀመጡም።
ደጋግ ሰዎች ዘወትር ከስፍራቸው አይነቃነቁም፤ ክፉዎች ግን በምድር ላይ አይኖሩም።
ነገር ግን ወደ መንገዴ እንደ ምመለስ እተማመናለሁ፤ እጆችም የነጹ ናቸውና፤ ደስታዬን አገኛታለሁ።
በሰማይና በምድር የተዋረዱትን የሚያይ፤
እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን።
እግዚአብሔር የርስቴ ዕድል ፋንታና ጽዋዬ ነው፥ ርስቴን የምትመልስ አንተ ነህ።
እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፤
አቤቱ፥ የመድኀኒቴ አምላክ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
እግዚአብሔር የግብዞችን አጥንቶች በትኖአልና በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤ እግዚአብሔር አዋርዶአቸዋልና አፈሩ።
ኃጥእ እንደ ዐውሎ ነፋስ ኅልፈት ይጠፋል፤ ጻድቅ ግን ተሰውሮ ለዘለዓለም ይድናል።
እነርሱም “ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል፤” አሉት።