ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፥ “ራስህን አድን፤ ወደ ኋላም አትመልከት፤ አንተንም መከራ እንዳታገኝህ በዚች ሀገር በዳርቻዋና በተራራዋ አትቁም።”
ፊልጵስዩስ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ስለ ክርስቶስ ያን ጥቅሜን ላጣው ወደድሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ይጠቅመኝ የነበረውን ሁሉ አሁን ለክርስቶስ ስል እንደ ጕድለት ቈጥሬዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ለእኔ ጥቅም የሚያስገኘውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ከዚህ በፊት ጠቃሚዎች ናቸው ብዬ አምንባቸው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ ስለ ክርስቶስ ብዬ ዋጋ እንደሌላቸው ከንቱ ነገሮች አድርጌ እቈጥራቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቍኦጥሬዋለሁ። |
ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፥ “ራስህን አድን፤ ወደ ኋላም አትመልከት፤ አንተንም መከራ እንዳታገኝህ በዚች ሀገር በዳርቻዋና በተራራዋ አትቁም።”
“ወደ እኔ የሚመጣ፥ ሊከተለኝም የሚወድ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሰውነት እንኳ ቢሆን የማይጠላ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ወገን ከሁሉ ያልወጣ፥ የእርሱ ገንዘብ ከሆነውም ሁሉ ያልተለየ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመሰገነው፤ ከብርሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓለማቸው ይራቀቃሉና።
የክርስቶስ የመስቀሉ ተግዳሮት ከግብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ባለጠግነት እንደሚሆን ዐውቆአልና፥ ዋጋውንም ተመልክቶአልና።