Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 23:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እውነትን ግዛ፥ አትሽጣትም፥ ጥበብንና ተግሣጽን፥ ማስተዋልንም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት፤ ጥበብን፣ ተግሣጽንና ማስተዋልን ገንዘብህ አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እውነትን ገንዘብህ አድርግ፥ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም ግዛ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እውነትን፥ ጥበብን፥ ተግሣጽን፥ ማስተዋልን ገንዘብ አድርጋቸው እንጂ አትተዋቸው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 23:23
19 Referencias Cruzadas  

የብልህ ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፥ የጠቢባን ጆሮም ዕውቀትን ትፈልጋለች።


“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፤ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።


ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። ዕውቀትንም ገንዘብ ማድረግ ከብር ይሻላል።


የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት ከግ​ብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚ​በ​ልጥ ባለ​ጠ​ግ​ነት እን​ደ​ሚ​ሆን ዐው​ቆ​አ​ልና፥ ዋጋ​ው​ንም ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና።


እና​ንተ የተ​ጠ​ማ​ችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ሂዱ፤ ገን​ዘ​ብም የሌ​ላ​ችሁ ሂዱና ግዙ፤ ብሉ፤ ያለ ገን​ዘ​ብም ያለ ዋጋም የወ​ይን ጠጅና ወተት ጠጡ።


ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናታል።


ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት።


ለአላዋቂ ሰው ገንዘብ ለምንድን ነው? አላዋቂ ሰው ጥበብን ገንዘብ ማድረግ አይችልምና፥ ቤቱን የሚያስረዝም ሰው ለራሱ ጥፋትን ይሻል፤ ለመማርም የሚጨንቀው ወደ ክፉ ይወድቃል።


እነርሱም በበጉ ደም በምስክራቸውም ቃል ድል ነሡት፤ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።


ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ፦ በየ​ከ​ተ​ማው መከ​ራና እስ​ራት ይጠ​ብ​ቅ​ሃል ብሎ ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል።


ሰነፎችን አትገሥጽ እንዳይጠሉህ፥ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios