ፊልጵስዩስ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደበትም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ክብር ጌታ እንደ ሆነ ያምን ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መላስ ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ እንዲመሰክሩ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንደበታቸውም “ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው” ብለው በመመስከር ለእግዚአብሔር አብ ክብር ይሰጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። |
በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፤ ይህም ስም እግዚአብሔር በነቢያት ኢዮሴዴቅ ብሎ የጠራው ነው።
ከሕዝቡ አለቆችም ያመኑበት ብዙዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ከምኵራብ አስወጥተው እንዳይሰዱአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም።
እንግዲህ እኔ መምህራችሁና ጌታችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኋችሁ እናንተም እንዲሁ የባልጀሮቻችሁን እግር ልታጥቡ ይገባችኋል።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ አለው፥ “የሚወደኝ ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፤ ወደ እርሱም መጥተን በእርሱ ዘንድ ማደሪያ እናደርጋለን።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ነገር ተናግሮ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አነሣና እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአልና ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው፤
ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ በእርሱ የሚያምን ቢኖር ከምኵራብ ይውጣ” ብለው አይሁድ ተስማምተው ነበርና።
እንግዲህ የእስራኤል ወገኖች ሁሉ እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም መሢሕም እንዳደረገው በርግጥ ይወቁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአልና፥ “እኔ ሕያው ነኝ፤ ጕልበትም ሁሉ ለእኔ ይሰግዳል፤ አንደበትም ሁሉ ለእኔ ይገዛል።”
አሕዛብም እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ ይቅር ብሎአቸዋልና፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ መካከል እገዛልሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ።”
ስለዚህም ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፥ “ኢየሱስ ውጉዝ ነው” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው” ሊል አንድስ እንኳን እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።
ለእኛስ ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ እኛም በእርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አለን።