ፊልጵስዩስ 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኵራት ስለ ክርስቶስ የሚያስተምሩ ግን፥ ይህን አድርገው በእስራቴ ላይ መከራ ሊጨምሩብኝ መስሎአቸው ነው እንጂ በእውነት አይደለም፤ በቅንነትም አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ ሳለሁ መከራ ሊያጸኑብኝ ዐስበው፣ በቅንነት ሳይሆን ለግል ምኞታቸው ሲሉ ክርስቶስን ይሰብካሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚያ የፊተኞቹ ግን በእስራቴ ላይ መከራን የሚያመጡብኝ መስሎአቸው፥ ያለ ንጹሕ ልቦና ከራስ ወዳድነት በመነሣት ስለ ክርስቶስ ያወራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያ ግን ስለ ክርስቶስ አጣምመው የሚሰብኩት በቅንነት ሳይሆን በራስ ወዳድነትና በእስራቴ ላይ ተጨማሪ ችግር ሊያመጡብኝ አስበው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ መከራን ሊያመጡብኝ መስሎአቸው፥ ለወገናቸው የሚጠቅም ፈልገው በቅን አሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስ ያወራሉ። |
አግሪጳም ጳውሎስን፥ “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ፈቅደንልሃል” አለው፤ ከዚህም በኋላ ጳውሎስ እጁን አነሣና ይነግራቸው ጀመር፤ እንዲህም አለ፦
ይህንም ስለ ራሱ ሲናገር ሀገረ ገዢው ፊስጦስ መለሰ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ፥ “ጳውሎስ ሆይ፥ ልታብድ ነውን? ብዙ ትምህርት እኮ ልብን ይነሣል” አለው።
ነገር ግን ምን አለ? በየምክንያቱ በእውነትም ቢሆን፥ በሐሰትም ቢሆን፥ ስለ ክርስቶስ ይናገራሉ፤ ሰውንም ሁሉ ወደ እርሱ ይጠራሉ፤ በዚህም ደስ ብሎኛል፤ ወደፊትም ደስ ይለኛል።
ስለ እናንተ ይህን ላስብ ይገባኛል፤ በምታሰርበትና በምከራከርበት፥ ወንጌልንም በማስተምርበት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባበራችሁ በልቤ ውስጥ ናችሁና።
በክርክርና ከንቱ ውዳሴን በመውደድ አትሥሩ፤ ትሕትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩ እንጂ አትታበዩ።